banner

ታክ ቢዝነስ ግሩፕ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ መሞያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ከቻይና ኩባንያ ጋር ተፈራረመ

#FastMereja I ታክ ቢዝነስ ግሩፕ እና የቻይናው የፋንግሊን ቡድን የኢትዮጵያን የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ስምምነት አደረጉ።

ዛሬ ሕዳር 02/2018 ዓ.ም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተካሄደ የስምምነት ፊርማ የኢትዮጵያ ታክ ቢዝነስ ግሩፕ ከቻይናው ፋንግሊን ግሩፕ ጋር በመተባበር ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢቪ) የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን በጋራ ለማልማት እና ለማስተዳደር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርሟል። ይህ አጋርነት የኢትዮጵያን አረንጓዴ የትራንስፖርት አጀንዳ በማራመድ እና የአገሪቱን ወደ ንፁህ እና ታዳሽ ኃይል ሽግግር በማፋጠን ረገድ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ተብሏል።

“ይህ አጋርነት ኢትዮጵያ ወደ ንፁህ ትራንስፖርት ጉዞ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል” ሲሉ የታክ ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቱጂ አማን ተናግረዋል። “ዓለም አቀፍ እውቀትን እና የአካባቢ ቁርጠኝነትን በማጣመር፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማስቻል ሰዎችንም ሆነ ፕላኔቷን የሚደግፍ የኢቪ መሠረተ ልማት ለመገንባት እንፈልጋለን” ብላል።

TAK ቢዝነስ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ያደረገ የጨው ማምረቻ፣ የቡና ኤክስፖርት፣ ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ፣ የሕክምና አቅርቦቶች፣ ኢነርጂ፣ የሪል እስቴት እና የቤት ዕቃዎች ምርትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ኩባንያ ነው።

#ቢዝነስበ





Leave a Comment