0
#FastMereja I የሁለገቡ ከያኒ ጌትነት እንየው የ68ኛ አመት የልደት በአልና የ43 ዓመታት የሙያ አገልግሎት የምስጋና መርሐ-ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተከብሯል።
ተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ ባዘጋጀው እና በርካታ የጥበብ ቤተሰበች በተገኙበት ልዩ የምስጋና መርሐ-ግብር ላይ አቢሲኒያ ባንክ ለከያኒ ጌትነት እንየው የ5 ሚሊዮን ብር ስጦታ አበርክቶለታል። ከዚህ በተጨማሪም ሌላኛው ተቋም ሀበሻ ቢራ አ.ማ የ2025 አዲስ BYD መኪና በስጦታ አበርክቶለታል።
ለአርባ ሶስት አመታት የሰራበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ካባ ያለበሰው ሲሆን አቢሲኒያ ባንክ በቅርቡ በ ባህርዳር ከተማ የሚከፍተውን ቅርንጫፍ ባንክም በጌትነት እንየው ስም መሰየሙን ይፋ አድርጓል። በዚህ ታላቅ መርሐ-ግብር ላይ ከያኒውን የሚዘክሩ ዝግጅቶች እና ምስክርነቶች ቀርበዋል።
Via: በፍቃዱ አባይ



