#FastMereja I ለ13 አመታት ሳይቋረጥ በኢቲቪ መስኮት ለህዝብ ሲደርስ የቆየዉ ቤቶች የቤተሰብ ሲትኮም 13ተኛ የምስረታ በአሉን በተለያዩ መርሀ ግብሮች ሊያከብር መሆኑን በዛሬዉ እለት በግራንድ ኤልያና ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
በ2005 ዓ.ም ጥር ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መተላለፍ የጀመረዉ ቤቶች ድራማ 13 ዓመታት ሳይቆራረጥ 525 ክፍሎችን በአንድ ጣቢያ ኢቲቪ ተወስኖ ለህዝብ ማድረሱ ለየት እንደሚያረገዉ ገልፀዉ በ13 አመት ቆይታዉ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሀገራዊ ጉዳዮች በመዳሰስ የሚያነሳቸዉ የህዝብ እና የመንግስት ጉዳዮች ከጭፍን ጥላቻ የራቁ እና ሚዛናዊ ትችቶች በመሆናቸዉ ተቀባይነታቸዉ እና ድራማዉን በነፃነት ለመስራት መንገዶችን እንዳመቻቸ ገልፀዋል።
ቤቶች በዚህ 13 ዓመታት ዉስጥ ተግባብቶ ለመስራት እና የጀመሩትን ለማስቀጠል ብዙ ፈታኝ ነገሮች ገጣሟቸዉ እንደነበር ገልፀዉ እነዛን መሰናክል በማለፍ ዛሬ ስኬቱ ላይ የደረሰ ድራማ መሆኑን ተዋናይ እና የድራማው ኘሮዲዉሰር ጥላሁን ጉግሳ ገልፀዋል።
በ13 ዓመታት ውስጥ የድራማው ተዋናይ የሆነችው አርቲስት ሰብለ ተፈራ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቷ ማለፉ ለቤቶች ድራማ ተግዳሮትን ቢፈጥርም ይህን ተግዳሮት ተቋቁሞ የድራማው ስርጭት ሳይቋረጥ መቆየቱንም አመልክቷል።
ቤቶች ድራማ የ13ኛ ዓመት በዓል ህዳር 27/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አድዋ ሙዚየም አዳራሽ በተለያዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች የ3 ሰዓት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል በሚያገኘዉ ዝግጅት የቤቶች ድራማ ስርጭት፣ የተዋንያኑ ቀጥታ የመድረክ ቴያትር፣ ጭውውቶች እና በሌሎች ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
#ኪነ_ጥበብ መረጃ




6 comments
እየታየ ነው እንዴ?
አለ እንዴ እስካሁን????
የጠነዛ😂😂🙆
በእግዚአብሔር ለወንድ ሥራ ካለ ፈልጉልኝ አባቴ አርፏል እኔ ተመርቀ ሥራ አጣው የቀን ሥራ እሰራ ነበር ግን ሥራ አንዴ ይኖራል አንዴ ደግሞ ይጠፋል ተቸገርኩ እናቴ ነበረች ፅዳት እየሰራች የሚታበላን አሁን ግን እሷም ትንሽ አሟት ተኝታለች በጣም ከፍቶኛል ቸግሮኛል😭 የትኛውንም ሥራ እሰራለው
የምትችሉ አስቤዛ መግዣም አግዙኝ 🙏 😭https://www.facebook.com/100088570536094/posts/796676323294712/?app=fbl
የቤቶች ድራማ ፋሽኑ ያለቀው ይቤና ማፊ ስወጠዉ ነው
Alle inde Ya Drama?😂
Inna Iriste ahunim lij nat.
Bezabih ahunim…….😂