banner

ከረጅም ቆይታ በኋላ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዳዊት መለሰ “ሚስጥር” በተሰኘው አዲስ አልበም ተለቀቀ

#FastMereja I ከኢትዮጵያ ተወዳጅ ድምፃዊያን መካከል አንዱ የሆነው ዳዊት መለሰ ከሁለት አስርትና ከዛ በላይ ዓመታት ካስቆጠረው የአልበም ስራ በኋላ “ሚስጥር” የተሰኘው አዲሱ አልበም ተመልሷል።

ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ላይ የተለቀቀው ሚስጥር አልበም፣ 11 ሙዚቃዎችን በውስጡ ያካተተ ሲሆን የዳዊት መለሰ አምስተኛው አልበሙ ነው። በናፍቆትና ፈውስ ላይ የተመሰረተው ይህ አልበም ፍቅርን፣ መራራቅን፣ ትውስታን እና እንደገና ለመጀመር የሚያስፈልገውን ጥንካሬን ይገልጻል።

በሙዚቃ አሬንጅመንት አበጋዝ ክብረወርቅ፣ ሚካኤል ኃይሉ እና ቢኒያም ተሳትፈውበታል።

የአልበሙ ምርቃት ከረዥም ጊዜ የኢንዱስትሪ አጋሮች በመሆን በልዩ የኮክቴል ድግስ ትናንት ምችት የተካሄደ ሲሆን ተጋባዥ እንግዶች በመጀመሪያ ከሚስጥር አልበም ውስጥ የተመረጡ ስራዎችን፣ በመቀጠልም ከሙዚቃው በስተጀርባ የነበረውን ሂደት ከዳዊትና የስራ አጋሮቹ ጋር በመሆን ታድመዋል።

የሙዚቃው በዳዊት መለሰ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ማሰራጪያ መተግበሪያዎች ላይ ተለቋል።

#ኪነ_ጥበብ





Leave a Comment