banner

በላይአብ ሞተርስ የተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሄደ

#FastMereja I በላይአብ ሞተርስ ዛሬ ሕዳር 09/2018 ዓ.ም በኔክስስ ሆቴል የተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሄደ።

መንግስት ያስቀመጠውን ፖሊሲ በመከተል በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ ገበያ እያቀረበ የሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ተሽከርካሪዎቹን አስመልክቶ በኩባንያው ባለሞያዎች እና የቻይና ኤክስፐርቶች በመድረኩ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንጌ ቦሩ በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከመቶ ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እየተንቀሳቀሱ ነው፣ በዚህም የአየር ብክለትን በመቀነስ እንዲሁም የነዳጅ ወጪን መቀነስ ተችሏል ብሏል። በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች አማራጭ ሆኖ ቀርበዋል፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአስመጪዎች የተለያዩ ማበረታቻዎች ማድረጉን ይቀጥላል ብሏል።

ዘመኑ ያፈራቸውን በታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ ገበያ እያቀረበ ነው ያሉት የበላይአብ ሞተርስ አቶ ምንተስኖት ተዘራ ከዶንግፊንግ ሞተርስ ጋር በመሆን በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ መኪኖችን በስፋት ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ገልጿል።

መርሃ ግብሩ ላይ በላይአብ ሞተርስ ከሲነርጂ ቴክኖሎጂ እና ዩቻአይ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።





Leave a Comment