banner

ህዳሴ ገበያ የገና ኤክስፖ 2018 እና የቲክቶክ ክሪየቲቪ አዋርድ የአጋርነት ስምምነት ፈጸሙ።

#FastMereja I ቅርንፉንድ ዲጂታል ማርኬቲንግ የተለያዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት፣ በማስተባበር እና በመምራት የሚታወቅ ድርጅት ነዉ የቲክቶክ ክሪየቲቪ አዋርድን በየአመቱ በማዘጋጀት እና በመሸለም የሚታወቅ ሲሆን የዘንድሮውን የ2018 ዓ.ም የቲክቶክ ክሪየቲቪ አዋርድ የፊታችን ቅዳሜ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በኮንቬክሽን ሴንተር እጩዎች ፣ ተሸላሚዎች ፣ ታዋቂ የኪነ -ጥበብ ባለሙያዎች ፤ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ፣የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሰነ-ስርዓት ይካሄዳል።

ይህንኑ ደማቅ የሽልማት ፕሮግራም አስመልክቶ እና የዚህ የሽልማት ፕሮግራም ዋነኛ ስፖንሰር የሆነው በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደው የዘንድሮው የ2018 ዓ.ም ህዳሴ የገና ኤክስፖ አዘጋጆች ስምምነት ፊርማ አካሂዷል።

በ92 ሚሊዮን ብር በማሸነፍ የዘንድሮ ህዳሴ ገበያ የገና ኤክስፖ 2018 ከታህሳስ 11-29/2018 ዓ.ም በኤግዚብሽን ማዕከል ይካሄዳል።

የኤክስፖ መግቢያ ቲኬት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና የሚያሸልም እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የህዳሴ የገና ኤክስፖ አስመልክቶ በቲክቶክ ቪዲዮ ለሚሰሩ ቲክቶከሮች የቲክቶክ ክሪየቲቪ አዋርድ መግቢያ ቲኬት እንደሚሸለሙ ተነግሯል።




Leave a Comment