#FastMereja I ዝግጅቱን የጣሊያን የንግድ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የጣሊያን የምግብ ሳምንት ተጠናቀቀ።
የጣሊያን የምግብ ዝግጅት ሣምንት የጣሊያን የምግብ ባህል ያስተዋወቀ አንዲሁም ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ወዳጅነት ያሳየ ሆኖ ተጠናቋል።
በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ለአራት ቀናት የተካሄደው መርሃ ግብሩ ሼፎችን፣ ተማሪዎችን፣ የመንግስት እና የቢዝነስ ሃላፊዎችን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተወካዮችን ማገናኘቱ ነው የተነገረው።
በዚህም የጣሊያንን የምግብ ባህል፣ልከኝነት አንዲሁም ብዝሃነት እንዲገነዘቡ አድል ፈጥሯል፡፡
በአዲስ አበባ የጣሊያን ንግድ ኤጀንሲ የንግድ ኮሚሽነር ክላውዲዮ ፓስኳሉቺ “የዘንድሮው የኢጣሊያ የምግብ ዝግጅት ሳምንት የወዳጅነት እና የጋራ እሴቶች ክፍ ብለው አንዲታዩ ያስቻለ “ነው ሲሉ ተናገረዋል፡፡
የጣሊያን ሼፎችን ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ተማሪዎች ጋር በማገናኘት የባህል ዲፕሎማሲውን እንዲጠናከር አድርገናል እንዲሁም በምግብ ጥናት እና ዝግጅት ዘርፍ አዳዲስ የትብብር ዕድሎችን ከፍተናል” ሲሉም አክለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ውስጥ፣ ተጋባዥ እንግዶች ፣ተማሪዎች በተገኙበት የጣሊያንን ባህላዊ እና ዘማናዊ ምግቦች የመጣጣም ዝግጅት ተካሂዷል፡፡
ታዋቂው ጣሊያናዊው ሼፍ ኤልያ ግሪሎቲ ኢትዮጵያውያን ሼፎች እና የምግብ ዝግጅት ተማሪዎች ስለ ምግብ ዝግጀት የተግባር ስልጠናዎችን እና ማሳያዎችን አቅርቧል።
በኢትዮጵያ የተካሄደው የጣሊያን የምግብ ሳምንት በህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ ለሚገኙ ህጻናት ማዕድ ማካፈልንም ያከተተ ሲሆን የጣሊያን ሼፎች ለልጆች ልዩ ጣፈጭ ምግብ አዘጋጅተው አቅርበዋል፡፡
በአጠቃላይ በሳምንቱ ውስጥ የተካሄዱት ወርክሾፖች፣ የምግብ ቅምሻ ፕሮግራሞች የጣሊያንን የምግብ አሰራር ያሳዩ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል በመስተንግዶ ዘርፍ ለልምድ ልውውጥ በር አንዲከፋት ያበረታታ ሆኖ አልፏል፡፡
የጣሊያን የምግብ ሳምንት ዓለም አቀፍ መርሃግብር ሲሆን አለማውም የጣሊያንን የምግብ አሰራር ለባህል የባህል ዲፕሎማሲ እና የምግብ ዘርፍ ወጪ ንግድን ማበረታታት ነው፡፡
#ኹነት





2 comments
ብሉ
እንዴ እኛ የት ነበርን ??
ቢያንስ መቅመስ ነበረብን