banner

ሰክሰስ ፕላስ ድርጅት በሲዳማ ክልል ለሚገኙ የአካል ጉዳተኞች 100 የዊልቸር ድጋፍ አደረገ።

#FastMereja I የስጦታ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ክብርት ሁሪያ አሊ በአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሠሩ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

የአካል ጉዳተኞችን መብት የማስከበር ፣ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ የሁሉንም ኃላፊነት ይጠይቃል ብለዋል። ሚኒስቴር መስሪያቤቱም ድጋፎች የታለመለትን አላማ እንዲያውሉ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ።

የሰክሰስ ፕላስ ሀገር በቀል የተራድኦ ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሬው በበኩላቸው ድርጅቱ ከተመሠረተ ሁለት አመት ያስቆጠረ ቢሆንም የአካል ድጋፍ መሳሪያዎችን በተለይም ዊልቸር በመስጠት ላይ እንዳለ ጠቁመዋል። የተጀመሩ ድጋፎችንም ለመቀጠል ቃል ገብተዋል።





Leave a Comment