#FastMereja I በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙን እናስታውቃለን፡፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተሰጡ መመሪያዎች መሠረት እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሕግ በተሰጠው የቁጥጥር ስልጣን መሰረት፣ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰረዛቸውን እንገልጻለን፡፡
የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ ሲሆን ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሀገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ሀገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል።
ለሚመለከታቸው አካላት የተላለፈ መመሪያ
1. ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች: –
ከታሀሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ ወዲያውኑ ማቋረጥ ይጠበቅባችኋል።
ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች (Deposit Gateways) አገልግሎት መስጠት ማቆም አለባቸው።
አዲስ ውርርድ መቀበል ፈጽሞ አይቻልም።
ሁሉም የሰርቨር መረጃዎችን፣ የፋይናንስ መዝገቦችን እና የተጠቃሚ መረጃዎችን በጥብቅ ጠብቀው የማቆየት ግዴታ አለባቸው። ማስረጃን ማጥፋት፣ መቀየር ወይም ማሸሽ በወንጀል ሕጉ መሰረት ያስቀጣል።
2. ለፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች፣ ፔይመንት ኢንስቱርመንት ኢሹወርስ እና ፔይመንት ሲስተም ኦፕሬተሮች): –
ከታሕሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ የሁሉም የውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ በመሰረዙ፣ በእናንተ በኩል የውርርድ ድርጅቶቹ የሽያጭ እንቅስቃሴ እንዳያከናውኑ እንድታደርጉ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እንደ ተቆጣጣሪና አስፈጻሚ አካል በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት፣ ይህን ውሳኔ ከሁሉም መንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር በጥብቅ ይከታተላል። መመሪያውን የሚጥስ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ ይሆናል።

9 comments
ኳስ ሚያይ ሰው ጠፋ በሉና😂
Good job 👏
Wayne score betting
ለምን እንዴ እረ ወድዛአአ
ጉሮሮህ ይዘጋ አቦ
ወይኔ ደህና ብር ሳልበላ
Nice Move!
Endeee
Ye zare kemeris 😭??
ትች አንዴም ሰልበላ