#FastMereja I 11 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ; ግብፅ; ሱዳን; ደቡብ ሱዳን; ጅቡቲ; ሶማሊያ; ኬንያ; ሩዋንዳ; ኡጋንዳ; ታንዛንያ; ቡሩንዲ) የሚገኙበት የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን 5 (ምስራቅ አፍሪካ) እንድትመራ ኢትዮጵያ በድጋሚ በፕሬዝዳንትነት በ11ዱ አባል ሀገራት በሙሉ ድምፅ ተመረጠች።
ዛሬ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም. በካይሮ St. Rigis Hotel በተካሄደው የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን 5 (ምስራቅ አፍሪካ) የምርጫ ኮንግረስ ስብሰባ ላይ ከተያዘው 3 አጀንዳዎች አንዱ በሆነው የዞን 5 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበትን በድጋሚ በሙሉ ድምፅ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጧል። ኮንግረሱ በዞኑ ስለተሰሩ እና በመሠራት ላይ ስላሉ ስራዎች የተወያየ እና ውሳኔም ማሳለፉ ታውቋል።
በኮንግረሱ የተገኙት የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝደንት በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ የአፍሪካን አንድነትና ጥቅም ማስከበር; በአንድነት ሁሉንም በስፖርታችን ማሳደግ እንዲሁም በአለምም መድረክ አንድ ሆነን መሠማት አለብን ብለዋል።
በማጠቃለያው የተናገሩት ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍትህ አኛ እዚህ የወከልነውን ትልቁን የተከበረው ህዝቦቻችንን ካሰብን በአህጉራችን ጥቅም አንድ መሆናችን እና ለአለም አንድነታችንን ማሳየቻችን ትልቅ ክብር ነው ብለው የዞን 5ቱ ኮንግረስ ተጠናቋል።
በነገው እና እሁድ የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን እና የአለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽ የምርጫ ኮንግረሶች ይካሄዳሉ። ለአፍሪካው ፕሬዝደንትነት ዶ/ር አሬሙ መንሰሩ (ቤኒን) እንዲሁም ለአለም አቀፉ ዶ/ር ሀሰን ሙስጠፋ (ግብፅ) በእጩነት መቅረባቸው ታውቋል።
#DrFeteh Weldesenbet #FastMereja



