banner

“አራት ነጥብ” የሚኪ ላላ የመጀመሪያ አልበም ተለቀቀ

#FastMereja I የድምጻዊ ሚኪያስ ንጉሴ (ሚኪ ላላ) “አራት ነጥብ” የተሰኘ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ተለቀቀ።

አልበሙ 13 ሙዚቃዎችን የያዘ ሲሆን ሚኪ ጃኖ ሙዚቃዎችን አቀናብሯል። ኤፍሬም አበበ (ከፍ ከፍ) አምስት ሙዚቃዎች ላይ በግጥም እና ዜማ ተሳትፏል፣ ቀሪዎቹን ሱራፌል የሺጥላ፣ ጥላሁን ሰማው፣ ዘርዓብሩክ ሰማሁ፣ ምህረት አሰፋ፣ ኢዮቤል ብርሃኑ ተሳትፏል።

ዞጃክ ወርልድ ዋይድ ሙዚቃውን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያሰራጭ ሲሆን በሚኪ ላላ እና በዞጃክ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በአለም አቀፍ የሙዚቃ ማሰራጭ መተግበሪያዎች ላይ ተለቋል።

ሶስት ሙዚቃዎች የቪዲዮ ክሊፕ ተሰርቶላቸዋል።

#ኪነ_ጥበብ መረጃ





Leave a Comment