0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት 5 ወራት ውስጥ ስራቸውን በአግባቡ ባልተወጡና በስነ-ምግባር ጉድለት በተገኙ 179 ሰራተኞች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
• የእርምጃው ምክንያት፦ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ጋር የተያያዙ ጥፋቶች እንዲሁም የስነ-ምግባር ግድፈቶች።
• የተቀጡ አካላት፦ 20 አመራሮች እና 159 ፈፃሚ ባለሙያዎች።
• የክትትል ዘዴዎች፦ በሰርቪላንስ ካሜራ፣ በምስለ ተገልጋይ እና በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የተገኙ ግድፈቶች ናቸው።
• የቀጣይ ትኩረት፦ በኢ-ፋይሊንግ፣ በኢ-ፔመንት እና በቲን ቁጥር አሰጣጥ ዙሪያ አገልግሎቱን በማዘመን የግብር ከፋዩን እንግልት መቀነስ።
ቢሮው በቀጣይም ጥብቅ ክትትል በማድረግ ገቢን በፍትሃዊነት የመሰብሰብ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

3 comments
Good job🙏🙏
Good👍
የምን እርምጃ 😳