banner

ወገናችንን ከረሃብ እልቂት ለመታደል የተጀመሩ የነፍስ አድን ስራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ተባለ

#FastMereja I ​በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች፣ ግለሰቦች፣ ማህበራት እና የመንግስት አካላት “በዓይናችን ፊት የሚረግፈውን ህይወት እንታደግ” በሚል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ወገኖች የጀመሯቸው የነፍስ አድን እንቅስቃሴዎች ሊጠናከሩ፣ ሊቀናጁ እና ወደ ተግባር ሊቀየሩ እንደሚገባ ተገለጸ።

​በሕፃፅ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በምግብ እና በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ወዲህ ብቻ ከ50 በላይ ተፈናቃዮች ሲሞቱ፣ በአጠቃላይ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ300 በላይ ተፈናቃዮች ህይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።

​አሁንም ቢሆን በምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ወገኖች በረሃብ እና በመድኃኒት እጥረት ምክንያት በየቀኑ ለሞት እየተዳረጉ እንደሚገኙ ተመልክቷል።

​የምዕራብ ዞን አስተዳደር፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች ወገኖች፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ግለሰቦች፣ ባለሀብቶች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ሰብአዊነት የሚሰማችሁ ሁሉ “ወገን ለወገን” በሚል ሰብአዊ ጥሪ አስቸኳይ እና የተቀናጀ እርዳታ በማድረግ ለዚህ ህዝብ እንድትደርሱ ጥሪ አቅርበዋል።





Leave a Comment