banner

ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያዊ ያልተከፈላቸው 50,000 የሳዑዲ ሪያል አንዲከፈላቸው ተደረገ።

#FastMereja I አቶ አብዱቃድር ሀሰን አሊ የተባሉ ኢትዮጵያዊ በህጋዊ መንገድ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ሄደው በጄዳ ከተማ በአንድ ካምፓኒ ውስጥ ሲሰሩ ከቆዩ በሗላ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን፣ ነገር ግን ሲሰሩበት ከነበረው Fast Food Company የአገልግሎት ክፍያ ሳይከፍላቸው ቆይቷል፣ በመሆኑ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ ድጋፍ እና ክትትል እንዲያደርግላቸው ከቤተሰቦቻቸው (ከወራሾቻቸው) በኩል በቆንስላ ፅ/ቤቱ የዜጎች ድጋፍና ክትትል የስራ ክፍል ጥያቄ አቅርበዋል።

በዚሁ መሰረት ጉዳዩ ላይ በተደረገ ክትትል ያልተከፈላቸው የአገልግሎት ክፍያ በድምሩ 50,000 (ሃምሳ ሺ የሳዑዲ ሪያል) እንዲከፈላቸው በማድረግ ለወራሾች እንድደርስ ማመቻቸት ተችሏል።

1 comment

Kalkidan Dawit December 23, 2025 - 10:47 am

ከሞቱ በኋላ የተከፈላቸውን ገንዘብ በምን ዘርፍ ኢንቨስት ሊያደርጉት አስበው ይሆን

Reply

Leave a Comment