#FastMereja I ጊፍት ሪል ስቴት “መኖር በጊፍት መንደር” በሚል መሪ ቃል የገና በአል የሽያጭ ኤክስፖ ከዛሬ ከታህሳስ 15 ጀምሮ እስከ ገና ዋዜማ ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም በለገሃር መንደር በይፋ ይካሄዳል።
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ግንባታቸው በፍጥነት በመካሄድ ላይ በሚገኙ በለገሃር፣ በተ/ሃይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በአትላስ፣ በሲኤምሲ እና በፈረስ ቤት ቅንጡ አፓርትመንቶችንና የንግድ ሱቆችን በ2% ቅድመ ክፍያ እስከ 20% በሚደርስ ቅናሽ 1000 ቤቶች ለሽያጭ ማቅረቡን ገልጿል።
ይህንን የጊፍት ሪል ስቴት የ2018 ዓ.ም የገና በዓል ኤክስፖ ሽያጭ እስካሁን ባለፉት ስምንት ወራት በተከታታይም ለአምስት ጊዜያት ከተካሄዱት ኤክስፖዎች ልዩ የሚያደርገው፣ በተሻለ አማራጭ፣ በተሻለ ዋጋ፣ የመኖሪያና የንግድ ቤት ባለቤት የማድረግ አጋጣሚን ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ጊፍት ሪል እስቴት መፍጠሩ መሆኑ ተገልጿል።
በባለፈው 2017 አመት በተዘጋጀው የሽያጭ ኤክስፖ ከ2500 ቤቶች በላይ መሸጣቸው ተገልጾ በዚህም 10 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱ ተገልጿል።
በመሆኑም የፈረንጆችን ክሪስማስ እና አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ እንዲሁም የኢትዮፕያን ገና በዓል ለማክበር ወደ ውድ እናት አገራቸዉ የመጡ እና በመምጣት ላይ የሚገኙ ውድ የውጭ እና የአገር ውስጥ አዳዲስ የጊፍት ደንበኞች፣ ይህንን መልካም አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።




