banner

ግብፅ የአሰብ እና ዶራሌህ ወደቦችን ለማልማት ስምምነት መፈፀሟ ተነገረ

#FastMereja I ግብፅ በኤርትራ እና በጅቡቲ የሚገኙ ስትራቴጂካዊ የወደብ ማልማት ስራዎችን ለመስራት መስማማቷን የካይሮ ምንጮችን ጠቅሶ አቡ ዳቢ የሚገኘው ዘ ናሽናል ጋዜጣ ዘግቧል። ይህም በመካሄድ ላይ ባለው የዓባይ ውኃ ውዝግብ ሳቢያ፣ ወደብ በሌላት ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫና እንደሚያበዛው ተጠቁሟል።

ግብፅ በሚስጥር በፈረመቻቸው ስምምነቶች መሠረት፣ በኤርትራ የሚገኘውን የዓሰብ ወደብን እንዲሁም በጅቡቲ የሚገኘውን የዶራሌህ የኤደን ባሕረ ሰላጤ ወደብን ለማዘመን ተስማምታለች። ይህም የወደቦቹን አቅም ከማሳደግ ባለፈ ለጦር መርከቦች የሚሆኑ መረገጫዎችን እንዲሁም ለጥቂት የልዩ ኮማንዶ ጦር አባላት ማረፊያ የሚሆኑ ተቋማትን መገንባትን ያካትታል ተብሏል።

ሁለቱም ወደቦች አውሮፓን፣ መካከለኛው ምስራቅን፣ እስያን እና ምስራቅ አፍሪካን የሚያገናኘው የቀይ ባሕር ደቡባዊ መግቢያና ወሳኝ የባሕር መስመር በሆነው በባብ ኤል-መንደብ አቅራቢያ ይገኛሉ።

ሁለቱንም አገራት [ኤርትራን እና ጅቡቲን] የምትዋሰነው ኢትዮጵያ፣ ለሸቀጦች ልውውጥ በከፍተኛ ሁኔታ በዶራሌህ ወደብ ላይ ጥገኛ ናት። በመሆኑም በዋናው የባሕር መውጫዋ በቀይ ባሕር ላይ ጎረቤት አገራት ግዛታዊ ወይም ወታደራዊ ይዞታ ለመመሥረት የሚያደርጉትን ጥረት ለረጅም ጊዜ ስትቃወም ቆይታለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በያዝነው ዓመት ህዳር ወር አጋማሽ በሰጡት አስተያየት፤ አስተማማኝ የአሰብ ወደብ አገልግሎት ተጠቃሚነት የኢትዮጵያ ተቀዳሚ ብሔራዊ እና ስትራቴጂካዊ ፍላጎት መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ንግግር ያደረጉት ህዳር 4/2018 ዓ.ም ሆርን ሪቪው እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ባዘጋጁት የውጭ ፖሊሲ መድረክ ላይ ነበር። በዚሁ መድረክ ላይ ሚኒስትሩ የኢትዮ-ኤርትራ ውጥረት ታሪካዊ እና ወቅታዊ ዳራዎችን በተመለከተ ዝርዝር ትንታኔ የሰጡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የምትከተለውን አቅጣጫም ገልጸዋል። ንግግራቸውም ጥያቄና መልስ በተካሄደበት የውይይት መድረክ የታጀበ ነበር።

ሚኒስትሩ የአሰብ ወደብን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፤ አሰብ ወደብ ለኢትዮጵያ ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህም የሆነው ታሪካዊ እና ሕጋዊ ስህተቶችን ለማረም ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ኤርትራ ከመገንጠሏ በፊትም ሆነ በኋላ በወደቡ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ስላፈሰሰበት ጭምር መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውበታል።

Via: አዲስ ስታንዳርድ

5 comments

Sewbe Tefera December 25, 2025 - 4:03 pm

እንተያያለና ትሞክረው

Reply
በምን ስበብ ልርሳት December 25, 2025 - 4:04 pm

ጦርነት ከማወጅ ቢበልጥ እንጂ አያንስም

Reply
Wesenu Damtew December 25, 2025 - 4:04 pm

ይሄን ትልቅ ተስፋችንን የህልውና ጥያቄያችንን ከምናጣማ የኢትዮጲያን ልክ ማየት ያለባቸው ይመስለኛል።🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Reply
እዮብ መኮንን December 25, 2025 - 4:04 pm

ግብፅ ፔሬዷ መጣ ደሞ

Reply
ሰልማን ሰይድ December 25, 2025 - 4:05 pm

መፈራረም ቀላል ነው መተግበር ግን እደወሬ ቀላል አደለም ጀግንነት ይጠይቃል

Reply

Leave a Comment