banner

ዝግባ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለገና በአል ድጋፍ አደረገ!

#FastMereja : ዝግባ የህጻናትና አረጋውያን የበጎ አድራጎት ድርጅት የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ወላጆቻቸዉን በሞት ላጡና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ፣ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸዉ አረጋዉያን፣ ለችግረኛ ሴቶች የመዓድ ማጋራት፣ የአልባሳት እና ቁሳቁስ ስጦታ በዛሬዉ እለት አካሂዷል።

በዛሬዉ እለት ከህፃናትና አረጋውያን እንዲሁም ከችግረኛ ሴቶች መካከል በአዲስ አበባ ድጋፍ የሚደረግላቸውን ከ2ዐዐ በላይ ሰዎች ነዉ በአልን ምክንያት በማድረግ ድጋፉ የተደረገዉ።

ይህ የድጋፍ እንክብካቤ እና የበጎነት ተግባርም የ2018ዓ.ም የገና በአልን ምክንያት በማድረግ የተካሄደ ነዉ።

በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ድጋፍ ላይ ድጋፍ ላደረጉ እና አብረዋቸዉ እየሰሩ ለሚገኙ ድርጅቶች ምስጋና በማቅረብ ለአባይ ባንክ እና ፀደይ ባንክ የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።

እንዲሁም ዝግባ የበጎ አድራጎት ድርጅት ኮሜዲያን ምትኩ ፈንቴ እና ኮሜዲያን አዝመራዉን በጎ ፈቃድ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

የድርጅቱ ስራ አስኪያጁ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው እንደገለፁት ሁሉም ግለሰብ እና ድርጅት ይህን ዘላቂ ድጋፍ ለሚሰጠዉ ድርጅት ድጋፋቸዉን እንዲሰጡ በመግለፅ እስካሁን አብረዋቸዉ ሲሰሩ ለቆዩት እየሰሩም ላሉት ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

በምሳ ፕሮግራሙ የተገኙት አረጋውያኖች ድጋፉን ላበረከተላቸው ድርጅት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

ዝግባ የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሀያ ሶስት ህፃናት እና ሀያ ሁለት አረጋውያንን በማቀፍ የተጀመረው ዝግባ የህጻናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ወላጆቻቸውን በሞት ላጡና ለችግር የተጋለጡ ህጻናት ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው አረጋውያን፣ ለችግረኛ ሴቶችና ለማህበረሰብ ክፍሎች የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት እየሰጠ ያለ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን አገልግሎቱን በባሕርዳር እንጅባራ እና በአዲስ አበባ እየሰጠ ይገኛል።





Leave a Comment