#FastMereja I በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሰፊ ልምድ ካለው አሸቶ ኢንጂነሪንግ ጋር በመተባበር ቺባን ፕሮፐርቲስ “አልፋ” የተሰኙ ባለ አምስት ኮከብ የሌግዠሪ አፓርትመንቶችን ሽያጭ ዛሬ በይፋ ጀምሯል።
በአዲስ አበባ ሃያ ሁለት (ሌክስ ፕላዛ ጀርባ) በሚገኘው ሳይት ላይ የተገነቡት እነዚህ አፓርትመንቶች፣ በ800 ካሬ ሜትር ላይ ያረፉና ከስቱዲዮ እስከ ባለ ሦስት መኝታ አማራጮችን ያካተቱ ናቸው።
የአፓርትመንቶቹ ልዩ መገልገያዎች፦
📌 ደረጃቸውን የጠበቁ ጂም፣ መዋኛ ገንዳ እና የልጆች ማጫወቻ።
📌 ዘመናዊ ሱፐርማርኬት፣ ሬስቶራንት፣ ካፌ እና ቅንጡ ሎቢ።
📌 የ24 ሰዓት የጥበቃ እና የቫሌት ፓርኪንግ አገልግሎት።
📌 ባለ አምስት ኮከብ የህንፃ አስተዳደር እና የሪሴፕሽን አገልግሎት።
አልፋ አፓርትመንት ከመኖሪያነት ባለፈ፣ በፓርትነርሽፕ ለሚሳተፉ ባለሀብቶች በየዓመቱ የ17 በመቶ የተረጋገጠ ገቢ የሚያስገኝ የኢንቨስትመንት ዕድል ይዞ ቀርቧል።
ይህን ፕሮጀክት እያከናወነ የሚገኘው አሸቶ ኢንጂነሪንግ፣ ቀደም ሲል የድሬዳዋ ስታዲየምን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ግዙፍ የህንፃ፣ የመንገድ እና የድልድይ ግንባታዎችን በማከናወን የሚታወቅ የደረጃ 1 ኮንስትራክሽን ድርጅት መሆኑ ተገልጿል። ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ባለ 15 ወለል (2B+G+15) የሪል ስቴት ግንባታ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።




