#FastMereja I አገልግል የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ከኮረንቲ አውቶ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር፣ የትራንስፖርት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የጀመረውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተሽከርካሪዎች ዛሬ በይፋ አስረክቧል።
በላምበረት አካባቢ በሚገኘው የኮረንቲ አውቶ ግቢ በተከናወነው በዚህ የርክክብ መርሃ ግብር ላይ፣ ለማህበሩ አባላት እና ለተለያዩ ግለሰቦች ለግል መጠቀሚያ እና ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ተላልፈዋል። ይህ ስምምነት ተሽከርካሪ ፈላጊዎች በተመጣጣኝ የቅድመ ቁጠባ መጠን እና በአነስተኛ ወለድ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
የኮረንቲ አውቶ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከአምራች ካምፓኒዎች ጋር ባለው አስተማማኝ ውል መሰረት የጥራት እና የመለዋወጫ ችግር የሌለባቸውን መኪኖች እያቀረበ ይገኛል። ተብሏል። በአሁኑ ወቅት በወደብ ላይ የሚገኙ ከ20 እስከ 37 የሚደርሱ ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን በሚቀጥሉት 45 ቀናት ውስጥ ለማስረከብ ሙሉ ዝግጅት መጠናቀቁንና ለዚህም የሁለተኛ ዙር ቅድመ ቁጠባ መጀመሩን አብስረዋል።
አገልግል የቁጠባና ብድር ተቋም በበኩሉ፣ በተለይም በከፍተኛ የተሽከርካሪ ዋጋ ምክንያት ስራ የሚፈቱ እና ያላቸውን ጥሪት የሚያባክኑ ወጣቶችን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጿል። ተቋሙ ከመኪና ብድር ባለፈ፦
• የቤት መስሪያና የቤት እቃ ማሟያ፣
• የንግድ ስራ ማስፋፊያ፣
• እና የልጆች ትምህርት ክፍያ የብድር አገልግሎቶችን ለአባላቱ እያቀረበ ይገኛል።
ይህ አጋርነት በታክሲ ማህበራት እና በተሽከርካሪ ፈላጊዎች ዘንድ በተደጋጋሚ ለሚነሳው የፋይናንስ እጥረት እንደ ትልቅ መፍትሄ የሚታይ ሲሆን፣ በቀጣይም ተደራሽነቱን በስፋት እንደሚቀጥል በመርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል።




