banner

አዋሽ ባንክ ለገና በዓል ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የማዕድ ማጋራት ድጋፍ አደረገ

​#FastMereja | በኢትዮጵያ የግል የባንክ ኢንዱስትሪ ቀዳሚ የሆነው አዋሽ ባንክ፣ “ክብራችን ወገናችን – ደስታችን ማካፈላችን” በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ.ም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ5ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ደጋፍ አደረገ።

​ባንኩ ዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሳሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባካሄደው መርሃ ግብር፣ አረጋውያን እና አቅመ-ደካማ ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል።

​የድጋፉ ይዘት ​ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ የተደረገው ድጋፍ በገንዘብ ሲሰላ ከ9,000 ብር በላይ ግምት ያለው ሲሆን፣ ​25 ኪሎ ግራም ዱቄት፣ ​5 ሊትር የምግብ ዘይት፣ ​3,000 ብር ጥሬ ገንዘብ ሲሆን ​ባንኩ ለዚህ ሀገር አቀፍ የበጎ አድራጎት ተግባር በድምሩ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን ገልጿል።

​ማህበራዊ ኃላፊነት እና ሰው-ተኮር ተግባራት
​አዋሽ ባንክ ላለፉት 31 ዓመታት በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ፈጠራ እና በአቅመ-ደካሞች ቤት ግንባታ ላይ በስፋት ሲሳተፍ ቆይቷል። ባንኩ ባለፈው የ2024/25 በጀት ዓመት ብቻ ለማህበራዊ ኃላፊነት አገልግሎቶች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መድቦ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑ ተገልጿል።

​ከበዓላት ድጋፍ ባሻገር፣ ባንኩ በተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች ፈጣን ድጋፍ በማድረግ እና በመንግስት የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን በማገዝ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።

​አዋሽ ባንክ በቀጣይም የህዝብ ወገንተኝነቱን በተግባር ለማሳየት የጀመራቸውን ሰው-ተኮር ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል።





Leave a Comment