banner

ድምጻዊ አንዱአለም ጎሳ በባለቤቱ ህልፈት ዙሪያ የተሰነዘሩበትን ውንጀላዎች አስተባበለ

#FastMereja I ድምጻዊ አንዱአለም ጎሳ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያና በተለያዩ ወገኖች በባለቤቱ በቀነኒ አዱኛ ህልፈት ዙሪያ እየተሰነዘሩበት ባሉ ትችቶችና ጥርጣሬዎች ላይ ምላሽ ሰጠ።

ድምጻዊው ዛሬ በአፋን ኦሮሞ ባወጣው የቪዲዮ መግለጫ፣ ክስተቱ የተፈጸመበትን ሁኔታና ከዚያ በፊት የነበሩ ጉዳዮችን በዝርዝር አብራርቷል በፋስት መረጃ በአማርኛ እንደሚከተለው ይቀርባል።

​አንዱአለም በመግለጫው ላይ እንደተናገረው፣ ባለቤቱ ቀነኒ አዱኛ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ራሷን የማጥፋት ሙከራ ታደርግ እንደነበር ገልጿል። ይህንንም አስቸጋሪ ሁኔታ ለቤተሰቦቿ በተደጋጋሚ እንዳሳወቀና አባቷ ጉዳዩን እንደሚያውቁ ተናግሯል።

​ባለቤቱ ህይወቷ ባለፈበት ዕለት ስለነበረው ሁኔታ ድምጻዊው የሚከተሉትን ነጥቦች አቅርቧል፦
በዕለቱ አብረው እንደነበሩና በተለይ ሃኪም ቤት የእርግዝና ምርመራ ስታደርግ፣ የልደት ፎቶ ልትነሳ ስትሄድም አድራሻት ስትጨርሺ ደውይልኝ ብያት ነው የሄድኩት ማታም አብረው ተኝተው እንደነበር ገልጿል።

ማታ አብረው ተኝተው ስለ ውሎ ስጠይቃት ከጎኑ ተነስታ መሄዷንና ስትቆይበት ተነስቶ ሲፈልጋት የኩሽናው በር በውስጥ በኩል ተቆልፎ እንዳገኘው ተናግሯል።

በሩ በላይ በኩል ክፍት ስለነበር ዘሎ ሲገባ “ላርጎ” (የጽዳት ፈሳሽ) ስትጠጣ ማየቱንና “ለምን እንዲህ ታደርጊያለሽ?” ብሎ ሊያረጋጋትና ሊያወራት መሞከሩን ገልጿል።

​ድምጻዊው እንዲህ ያለውን ድርጊት የማታቆም ከሆነ ለቤተሰቦቿ ነግሮ እንደሚለያዩ ቢነግራትም፣ እሷ ግን “ይስፋልህ” በማለት በድንገት ሮጣ መዝለሏን አስረድቷል። ሊይዛት ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቶ መውደቋን ገልጿል።

​ድምጻዊ አንዱአለም ጎሳ በማጠቃለያው ላይ “በምንም ተአምር እሷን አልገደልኳትም” በማለት የቀረበበትን የወንጀል ክስ አጥብቆ አስተባብሏል።

ሽማግሌዎችንም የላኩት ከቤተሰብ ጋር ያለው ግኑኝነት እንዲቀጥል በማሰብ እንጂ ካሳ ለመክፈል የሚባለውን ነገር አላውቅም ብሏል።

1 comment

Delay Selam Tg January 2, 2026 - 6:25 pm

የጎሳ ጉዳይ እዛው አባገዳ ይጨርሰው እኛ ብሄረሰቦች አያገባንም።

Reply

Leave a Comment