banner

ልጅ ተመስገን የሙዚቃ አልበም ሊለቅ ነዉ!

#FastMereja : ታዋቂው ኬሮግራፈር (የዳንስ ባለሙያ) ልጅ ተመስገን “ኢቲዲኤም ቢትስ” የተሰኘ በአይነቱ የተለየና የመጀመሪያው የሆነ የሙዚቃ አልበም አጠናቆ ለሙዚቃ አድማጩ ሊያደርስ መሆኑ ተገልጿል።

“ኢቲዲኤም ቢትስ” የሙዚቃ አልበም አዲስ የሙዚቃ ዘውግን የያዘና የኢትዮጵያን የተለያዩ ባህላዊ ሙዚቃዎችን ከዘመናዊ ሙዚቃ ጋር በማዋሃድ የተሰራ ሲሆን የ17 ብሄር ብሄረሰቦች ባህላዊ ሙዚቃዎች ከዘመናዊ ሙዚቃዎች ጋር ተዋህደውበታል።

13 ትራኮችን የያዘውና ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች የተሰሩለት ይህ አልበም የኢትዮጵያን ባህላዊ የሙዚቃ ዘውጎች ለአለም አቀፍ የሙዚቃ ኢንደስትሪው ለማስተዋወቅ ታስቦ የተሰራ ሲሆን የእያንዳንዱ ሙዚቃ ይዘትም የባህል ውክልናን የያዘ ነው።

ይህ በአይነቱ ለየት ያለ የሙዚቃ አልበም የኢትዮጵያን ባህል እና ወግ ለአለም ለማስተዋወቅ ትልቅ አስተዋፅ እንደሚኖረው ተገልጿል።

አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሁለት አመት ከሶስት ወር ወስዷል እንዲሁም ሰኞ ጥር 5 እንደሚመረቅ እና አርብ ጥር 8/2018 ዓ.ም ለአድማጭ እንደሚደርስ ተገልጿል።

ልጅ ተመስገን በኬንያ፣ በአልጄሪያ፣ በህንድ፣ በሱዳን፣ በናይጄሪያ እና በዩናይትድ ስቴትስ በስራዎቹ የተዘዋወረ ሲሆን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የክብር እንግዳ ሆኖ አስተምሩአል።

በተጨማሪም ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ የተደረገውን የአቀባበል ዝግጅት ላይ ተሳትፏል።





Leave a Comment