banner

ኒው ዌይ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት አርቲስት ቸርነት ፍቃዱን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

#FastMereja I አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ ከ ኒው ዌይ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት ጋር የብራንድ አምባሳደርነት የስራ ውል ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርሟል::

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው የአርቲስቱ የአምባሳደርነት ስምምነት የሚቆየው ለአንድ አመት ነው::

እንዲሁም አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ በ ኒው ዌይ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት ለቴሌቪዥን፤ቢል ቦርድ እና ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት መፈራረሙ ተጠቁሟል፡፡

ኒው ዌይ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት ከአርቲስት ቸርነት ፍቃዱ ጋር የተለያዩ ማህበራዊ ግዴታዎቻችንን ለመወጣት እና ህዝቡ ጋር የነበረውን ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ለማጎልበት የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ስምምነቱን እንዳደረገ ተነግሯል::

አርቲስቱ የተመረጠበት ምክንያቶችም ማህበራዊ ግዴታዎቹን በተገቢው የሚወጣ ስራው ላይ ብቻ የሚያተኩር ስለሆነ ነው ተብሏል::

የኒው ዌይ ትሬዲንግ ኃ. የተ. የግ. ማህበር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዋሲሁን ዘውዱ ዘገዬ እንደገለፁት ኒው ዌይ ኢትዮጵያ ከተመሰረተ 2 ወርን ያስቆጠረ ሲሆን በአርሜኒያ እና ጆርጂያ ውስጥ በሚገቡ ቱሪዝም እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶችን በማቅረብ በውጭ አገር በሚደረጉ ቱሪዝም ዘርፍ የሚሰራ ድርጅት ነው

አቶ ዋሲሁን አክለውም ከ2026 ጀምሮ ኩባንያው ከአርሜኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በዓለም ዙሪያ ታዋቂ በሆኑ ዋና ዋና የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመማር የትምህርት ጉዞዎችን ለማከናወን እየሰራ ይገኛል ብለዋል

ኒው ዌይ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቁ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች ላይ በመመስረት የኮርፖሬት ቱሪዝምን ለማደራጀት የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት የተከፈተ አስጎብኚ ድርጅት ነው።





Leave a Comment