#FastMereja I የአዲስ አበባ ቻንግ_ሁን ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ አሶሴሸን ከአዲስአበባ ወጣቶች እና ስፖርት ጋር በመተባበር ሲያካሂድ የነበረው 1ኛ ደረጃ የዳኝነት እና የአሰልጣኝነት ስልጠና ከ300 በላይ ዳኞችና አሰልጣኞች ከ30 በላይ ክለባት በማሳተፍ ስልጠና በመስጠትና በማጠናቀቅ በዛሬዉ ዕለትእሁድ (ጥር 17/2018 ዓ.ም.) ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በአራት ኪሎ ስፖርት እና ትምህርት ማእከል(ወወክማ)ማሰልጠኛ አዳራሽ ተመረቁ።
ለ15 ቀናት በተካሄደው የዳኞች እና የአሰልጣኞች ስልጠና እንደተመላከተዉ የስልጠናው ዋና ይዘት ትውልዱ በአካል በአእምሮ በስነ ምግባር በመንፈስ ጠንካራ እና አምራች ዜጋ እንዲሆን የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር የፍልሚያ አሸናፊ ሳይሆን በህይወት ፈተና ዉስጥ በብቃት ማሸነፍ የሚያስችል መሆኑተነግሮለታል።
ከዚህም ባሻገር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንተርናሽናል ቴኳን-ዶ ፌዴሬሽን ለአባል ክለባት ዳኞች እና አስልጣኞች ለተከታታይ 15 ቀናት በዳኝነት ስነ-ምግባር እና በዳኝነት ህግ እና ደንብ ዙርያ በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ ሲሰጥ የነበረውን ዓለም አቀፍ የዳኝነት ስልጠና በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ ተብራርቷል።
የዓለም ሻምፒዮና የተወዳዳሪዎች ማጣሪያ ለማድረግ ከ300 በላይ ለሚደርሱ ዳኞችና አሰልጣኞች ነዉ ስልጠና የተሰጠዉ።
የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽንና የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በመጪው ሰኔ ወር በደቡብ ኮሪያ ለሚካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የተወዳዳሪዎች ማጣሪያ ለማድረግ የዳኝነት (የአሰልጣኝነት)ስልጠና ከ300 በላይ ለሚደርሱ ሰልጣኞች ለ15 ቀናት ስልጠና የሰጣቸዉ በቅርቡም ምልመላ እንደሚካሄድ ተብራርቷል።
የኢትዮጵያ ቻንግ ሆን ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ኤልያስ ኩመል የ6 ዳን(ጥቁር ቀበቶ)ባለቤትና “እህቴን”የተሰኘ ፊልም ፕሮዲዩሰርና በመተወን የሚታወቁ ሲሆን”የጥበብ መንገድ” የተሰኘ መፅሐፍ በማዘጋጀትና በማሳተም በቴኳንዶ ጥበብ ደማቅ አሻራ ማስቀመጥ የቻሉ ባለሙያ ጭምር ናቸዉ።
በምረቃው ስነስርዓት ላይ ሰልጣኞች ስልጠናዉን ከመወጣት ባሻገር አስደናቂ የቴኳንዶ ትዕይንት አሳይተዋል።




