banner

በሊቢያ ስደተኞችን በማሰቃየት እና 2.1 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የተጠረጠሩ 28 ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው

#FastMereja I ​የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በሰው ልጅ መነገድ፣ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሕገ-ወጥ ሐዋላ ወንጀሎች በተሳተፉ 28 ተከሳሾች ላይ ክስ መመሥረቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ዛሬ ጥር 19/2018 ዓ.ም. አስታወቀ።

​ተከሳሾቹ ስደተኞችን በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ ካዘዋወሩ በኋላ፣ በመጋዘን አጉረው በማሰቃየት እና ድርጊቱን በቪዲዮ ቀርጾ ለቤተሰቦች በመላክ ከፍተኛ ገንዘብ ሲቀበሉ ቆይተዋል።

​በሕገ-ወጥ ዝውውሩ ከተሳተፉ 1,800 ስደተኞች መካከል የሁለቱ ሕይወት ሲያልፍ፣ የ15ቱ ደረሰበት አልታወቀም፤ ሌሎች ደግሞ ለከባድ ሕመም ተዳርገዋል።

​ስምንት ዋና ዋና ገንዘብ ሰብሳቢዎች ብቻ በባንክ ሂሳባቸው 2.16 ቢሊዮን ብር መሰብሰባቸው ተረጋግጧል።

​መንግሥት ከተከሳሾቹ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቤቶች፣ ተሽከርካሪዎች እና ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ለካሳ እንዲውል አግዷል። ምርመራው በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እንዲሁም በፋይናንስ ደኅንነት ተቋማት ቅንጅት የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

Leave a Comment