banner

የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ፍራንስኮ አሪዞ በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከልን ጎበኙ

#FastMereja I የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ፍራንስኮ አሪዞ እና በሮተሪ ኢንተርናሽናል አማካኝነት ህክምና ያገኙ ታካሚዎች በዛሬዉ እለት በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ተገኝተው ጉብኝት እና ምክክር አካሂደዋል።

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲያከናውን ድጋፍ ከሚያደርጉ ተቋማት መካከል የሆነው ሮተሪይ ኢንተርናሽናል (Rotary International) ከ1955 ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ረጅም እና ንቁ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ሮተሪይ ኢንተርናቲናል በጤና ዘርፍ ላይ ትኩረት በማድረግ በተለይም በበሽታ መከላከል፣ በእናቶችና ህፃናት ጤና እና በንጽህና (Sanitation) ዘርፎች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ እና በአሁኑ ወቅትም በኢትዮጵያ 21 የሮተሪይ ክለቦች እንዲሁም የሮተሪይ እና Interact ክለቦች ያሉት ሲሆን እነሱም ከኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር በትልቅ ደረጃ የጤና ፕሮጀክቶችን ለመፈጸም እየሰሩ እንደሚገኙም ነዉ የተገለፀዉ፡፡

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ላለፉት 36 ዓመታት ከ 9ሺህ በላይ ለሆኑ ታካሚዎች የነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎቶችን ሲሰጥ የቆየ ሀገር በቀል ለትርፍ ያለተቋቋመ ተቋም ነው።

ተቋሙ ከሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች ለሚመጡ ሁሉን ያካተተ የልብ ሕክምና አገልግሎት ከክፍያ ነጻ በመስጠት ላይ ይገኛል::

ከዚህም ባሻገር በዘርፉ የስለጠነ የጤና ባለሞያዎችን በማፍራትና ለልዩ ልዩ የትምህርት ማዕከላትን እንደ መመማሪያ መዳረሻ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን ማዕከሉ በሚሰጠው አገልግሎትም ቤተስቦችን ከሥነ ልቦና ከማኅበራዊ እና ከኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን መታደግ ተችሏል።

ድርጅቱ ሁሉንም የህክምና ወጪዎች ያለምንም ክፍያ በነፃ የሚያከናዉን ሲሆን አስፈላጊ ወጪውችን ከህብረተሰቡ በሚሰበሰብ ዕርዳታ፤ ከሀገር በቀል እና የዉጪ ድርጅቶች በሚደረግ ድጋፍ በመሸፈን ላይ ይገኛል፡፡





Leave a Comment