banner

የፍቺ መጠን 54 በመቶ ጭማሪ አሳየ

#FastMereja I በአዲስ አበባ ከተማ የትዳር ፍቺ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ54 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መረጃ ማስረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ቤዛዊት ብርሃኔ ከሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 6 ወራት 5 ሺህ 805 ባለትዳሮች ፍቺ ፈጽመዋል ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ54 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ በኩል የተከናወኑ ፍቺዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

በፍቺ ከተለያየው 5ሺህ 805 ቤተሰብ ውስጥ በአማካኝ በአንድ ቤተሰብ ሁለት ሕፃናት እንደሚኖሩ የተገለጸ ሲሆን 668 ሕፃናት ከአንደኛው ወላጃቸው ጋር ብቻ ለማደግ ተገደዋል ተብሏል፡፡

የቤተሰብ መበተን በውስጡ የሚኖሩ ሕፃናት ለተለያዩ ማኅበራዊ ቀውሶች እንዲዳረጉ ያደርጋል ያሉት ወ/ሮ ቤዛዊት፤ ባለትዳሮች ፍቺ ከመፈጸማቸው በፊት የልጆቻቸውን ቀጣይ እጣ ፈንታ ቆም ብለው እንዲያስቡ መክረዋል።

የጋብቻ ሁኔታን በተመለከተ ባለፉት 6 ወራት 19 ሺህ 800 ጋብቻዎች መመዝገባቸውን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል ሲል አሃዱ ሬዲዮ ነው የዘገበው።

Leave a Comment