#FastMereja I ከትናንት (ፌብራሪ 2 ቀን 2026) ጀምሮ በእንግሊዝ ውስጥ ትልቁ የወሲብ ድረ-ገጽ የሆነው ፖርንሀብ እና መሰል ድረ-ገጾች (እንደ ዩፖርን እና ሬድቲዩብ ያሉ) ለአዳዲስ ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት አቁመዋል። ይህ ውሳኔ የተላለፈው የእንግሊዝ መንግስት ባወጣው አዲስ የኢንተርኔት ደህንነት ህግ (Online Safety Act) ምክንያት ነው።
ለአዳዲስ ተጠቃሚዎች የተጣለ ገደብ፦ ከፌብራሪ 2 ጀምሮ ማንኛውም አዲስ ተጠቃሚ በእንግሊዝ ውስጥ ሆኖ እነዚህን ድረ-ገጾች በነፃነት መክፈት አይችልም። ድረ-ገጾቹን መጠቀም የሚችሉት ከዚህ ቀደም አካውንት የነበራቸውና እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆኑን ያረጋገጡ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው።
ህጉ ድረ-ገጾቹ ተጠቃሚዎቻቸው ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ጥብቅ መቆጣጠሪያ (ለምሳሌ፦ በክሬዲት ካርድ፣ በፓስፖርት ወይም በፊት መታወቂያ ቴክኖሎጂ) እንዲጠቀሙ ያስገድዳል።
የፖርንሀብ እናት ኩባንያ የሆነው አይሎ፣ የእንግሊዝ መንግስት የዘረጋው ስርአት “ውድቅ የሆነ ስርአት” ነው ሲል ወቅሷል። ኩባንያው እንደሚለው፣ ይህ ህግ ተጠቃሚዎች ይበልጥ ደህንነታቸው ወደማይጠበቅና ቁጥጥር ወደሌለባቸው የኢንተርኔት ክፍሎች (unregulated sites) እንዲሄዱ ያደርጋል የሚል ስጋት አለው።
የእንግሊዝ መንግስት እና የመገናኛ ብዙኃን ተቆጣጣሪው (Ofcom) ህጉ የተረቀቀው ህፃናት ያለ እድሜያቸው ለወሲባዊ ምስሎችና ቪዲዮዎች እንዳይጋለጡ ለመከላከል መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያም ከጥቂት ዓመታት በፊት ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዷ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ የሞራል እሴቶችን ለመጠበቅ እና ታዳጊዎችን ከአልባሌ ምስሎች ለመታደግ በሚል የወሲብ ድረ-ገጾች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይከፈቱ በቋሚነት መዝጋቱ ይታወሳል።
