0
#FastMereja I ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያስመዘገበውን ታላቅ የአቅም ግንባታ ይፋ አደረጉ።
ለውጡ ሲመጣ የአየር ኃይሉ የነበረው አንድ የሚበር ሄሊኮፕተር ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ ላይ ግን ለተለያዩ ተግባራት የሚውሉ ከ100 በላይ ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት መሆኑን ገልጸዋል።
የአየር ኃይሉ ግንባታ “ባንዳን ከማቁሰል ባለፈ” የሀገሪቱን ምሰሶ የሚገዳደሩ ኃይሎችን ለመመከት እና ኢትዮጵያን ለማጽናት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
”ከባንዳዎች የበለጠ ሀብት ካላመነጨን በዲፕሎማሲና በሚዲያ ጫና ይፈጠርብናል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መፍትሔው ብቃትን ማሳደግና ጠንክሮ መገኘት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያን መጉዳት የሚፈልጉ ኃይሎች ምንም ያህል የገንዘብ ድጋፍ ቢደረግላቸውም፣ ሀገሪቱን የሚያቆሙበት አቅም እንደሌላቸውም አስታውቀዋል።
