#FastMereja I በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ በዜማዎቻቸው ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ገጽ መስተጋብራቸው (Social Media Engagement) ተወዳጅነትን እያተረፉ የመጡ ድምፃውያን ቁጥር እየጨመረ ነው። ከእነዚህ መካከል ደግሞ ሳሚ ዳን ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
ሳሚ ዳን በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ፖስቶች ላይ የሚሰጣቸው ምላሾች (Replies) እና ቀልድ የቀላቀሉ አስተያየቶች፣ አድናቂዎቹ ዘንድ “ከሙዚቃው እኩል” የሚጠበቁ እስከመሆን ደርሰዋል። ይህንን ተከትሎም አሁን ላይ ሌላኛው ታዋቂ ድምፃዊ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ) በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ ፖስቶች ላይ በስፋት ኮሜንት ማድረግ መጀመሩ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
ይህንን የልጅ ሚካኤልን አዲስ እንቅስቃሴ የተመለከተው ሳሚ ዳን፣ በራሱ የፌስቡክ ገጽ ላይ እንዲህ ሲል በጨዋታ መልክ ገልጾታል፦
“እና ሁሏም መኮመት ጀመረች ማለት ነው..😂 Sami-Dan effect..”
ለምን ትኩረት ሳበ?
ሳሚ ዳን በኮሜንቶቹ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ተጫዋች መሆኑ ለአርቲስቶች አዲስ የደጋፊ ማፍሪያ መንገድ (Fan Base Engagement) ሆኗል።
ልጅ ሚካኤል (ፋፍ) በባህሪው ተጫዋች ቢሆንም፣ ሰሞኑን በተለያዩ ፖስቶች ላይ የሚሰጣቸው አስተያየቶች በደጋፊዎች ዘንድ በፈገግታ ታይቷል።
