0
#FastMereja I አዋሽ ባንክ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የ”ደንበኞች ሳምንት” መርሃ-ግብር ዛሬ በዋናው መስሪያ ቤት በይፋ አስጀመረ። ለአንድ ሳምንት የሚቆየው ይህ መርሃ-ግብር በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች ይተገበራል።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለጹት፣ ባንኩ በአሁኑ ወቅት የቅርንጫፎቹን ብዛት ከ1,000 በላይ ማድረስ የቻለ ሲሆን፣ በቅርቡም 1,000ኛውን ታሪካዊ ቅርንጫፍ በኤጀርሳ ጎሮ ከተማ መርቋል።
ባንኩ በዲጂታል የክፍያ ስርዓት ዘርፍ ባሳለፍናቸው 6 ወራት ብቻ አንድ ትሪሊየን ብር የሚጠጋ የክፍያ ልውውጥ መከናወኑን አስታውቋል።
ባንኩ በ24 ሰዓት ዲጂታል ቅርንጫፎች፣ በአዋሽ ብር ፕሮ፣ በኤቲኤም እና በኢንተርኔት ባንኪንግ አማካኝነት ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ደንበኞች ቅሬታና አስተያየታቸውን በ8980 ነፃ የጥሪ ማዕከል እና በኦንላይን አማራጮች ማድረስ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ይህ ሳምንት ደንበኞችን ለማመስገንና በሰራተኞች ዘንድ የላቀ የአገልግሎት አሰጣጥ መንፈስን ለማስረጽ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።




