banner

የኢትዮጵያን የትምህርት ቴክኖሎጂ ለማጠናከር የሚያግዝ መድረክ ተካሄደ!

#Fastmereja I ሪች ፎር ቼንጅ የተሰኘ ተቋም ያዘጋጀውና የሀገሪቱን የትምህርት ቴክኖሎጂ (EdTech) ሥነ-ምህዳር ለማጠናከር ያለመ ከፍተኛ የሥራ ጉብኝትና የፈጠራ ውጤቶች የቀረቡበት መድረክ በዛሬዉ እለት ተካሂዷል።

በመድረኩ ባለሀብቶችን እና የስነ-ምህዳር ተዋናዮችን በመሰብሰብ በዲጂታል ትምህርት፣ በፈጠራ መር ሥራ ፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ላይ በተመሰረቱ መፍትሄዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በዘርፉ የተመረጡ ኢትዮጵያውያን የትምህርት ቴክኖሎጂ (EdTech) ሥራ ፈጣሪዎች የትምህርትን ተደራሽነት፣ ጥራትና ፍትሃዊነት ለማሻሻል የቀረጹዋቸውን የፈጠራ መፍትሔዎች ለባለሀብቶችና ለፖሊሲ አውጭዎች አቅርበዋል።

እንዲሁም በዲጂታል ትምህርት፣ በኢኖቬሽንና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ዙሪያ በሚመለከታቸው አካላት መካከል ሰፊ የልምድ ልውውጥና የኔትወርክ ትስስር ተደርጓል።

መድረኩ የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የቴክኖሎጂና የዓለም አቀፍ አጋርነት ያለውን ሚና ያጎላ እንደሆነ ተገልጿል።

ከፍተኛ የስዊድን የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት መሠረት በማድረግ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ፣ የሪች ፎር ቼንጅ ዓለም አቀፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሶፊያ ብሬትሆልትዝ፣ በኢትዮጵያ የስዊድን ኤምባሲ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ሪች ፎር ቼንጅ (RFC) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ መንግስታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ዋና መሥሪያ ቤቱ በስቶክሆልም፣ ስዊድን ያቋቋመ ነው፡፡





Leave a Comment