banner

“ፍካሬ ትኩረት” የተሰኘ መፅሐፍ ተመረቀ

#Fastmereja: በዲጂታል ዘመን የተጋረጠብንን ረቂቅ ወረራ በጥልቀት የሚመረምረው የአብዲበሽር ሰይድ ዶ/ር ሁለተኛ መፅሀፍ የሆነዉ “ፍካሬ ትኩረት” የተሰኘዉ መፅሀፍ በዛሬዉ እለት ተመርቆ ለአንባብያን በቅቷል።

ይህ መፅሀፍ በዲጂታል ዘመን ትኩረታችን እንዴት ለኃያላን ኩባንያዎች የገቢ ምንጭ እየሆነ እንደሆነ፤በማንነት እና በዲጂታል ልማት መካከል ስላለው ቁርኝት፤የሀገራትን የኃያልነት ሽኩቻ አዲስ መልክ በጥልቀት የሚዳስስ እንደሆነ ነዉ የተገለፀዉ።

መፅሀፉ 107 ገፆች እና 7 ምዕራፎችን የያዘ ሲሆን ሁለቱ ምዕራፍ ሁለት የተለያዩ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘ እንደሆነ ተገልጿል።

የመፅሀፉ አላማ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ማንነታችን ድረስ ይሄዳል ወይ? ለሚሉ ጥያቄዎች የዉይይት መድረክ መክፈት መሆኑ ነዉ የተነገረዉ።

እንዲሁም በመፅሀፉ ዙሪያ በምሁራን እና በስነ-ፅሁፍ ባለሙያዎች የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የዚህ መፅሀፍ ፀሀፊ አብዲበሽር ሰኢድ ዶ/ር የይንቨርስቲ መምህር እና የምርምር ስራ በመስራት የሚታወቅ ሲሆን ቀደም ሲል “Architects of The Ummah” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይታወቃሉ።





Leave a Comment