#FastMereja I ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም (DIGAF MFI) ከደንበኞቹ የሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገለጸ። ተቋሙ ይህንን ስኬት ያስመዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ በግለሰቦች፣ በደመወዝ ከፋዮች እና በንግድ ድርጅቶች ዘንድ ያለውን አመኔታ በማሳደጉ መሆኑን አመልክቷል።
ይህ የተመዘገበው ውጤት ተቋሙ ለተደራጀ የፋይናንስ አስተዳደር፣ ለኃላፊነት የተሞላ የብድር አሰጣጥ እና ለዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶች የሰጠው ትኩረት ውጤት መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በቴክኖሎጂ የታገዘ የብድር ሞዴልን በመከተል ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረጉ ለተቀማጭ ገንዘብ እድገቱ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል።
የድጋፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ቱሪ ባደረጉት ንግግር “ይህ ስኬት የገንዘብ ብልጫ ብቻ ሳይሆን፣ ደንበኞች በተቋሙ ላይ ያላቸውን እምነት የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው።” ብሏል።
ተቋሙ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ኃላፊነት የሚሰማው የዲጂታል ብድር አሰጣጥን እና የፋይናንስ አካታችነትን ለማጠናከር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ባለፉት ዓመታት መደበኛ የኢኮኖሚ ዘርፍ ተሳታፊዎችን እና የደመወዝ ከፋዮችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የፋይናንስ አማራጮችን በማቅረብ ላይ ትኩረት አድርጎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወሳል።




