0
#FastMereja I በየቀኑ ነዳያንን በመመገብ የሚታወቀው አገር በቀል ድርጅት የእማማ ዝናሽ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ዛሬ በመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ደማቅ የነዳያን ምገባ መርሃ ግብር አካሂዷል።
በዕለቱ በተከናወነው በዚህ የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ በርካታ በጎ ፈቃደኞች በጉልበታቸውና በሙያቸው ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ የደብሩ የቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላትም በንቃት በመሳተፍ ለዝግጅቱ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።




