0
#FastMereja I የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በውጭ ሀገር ሲከታተሉ የነበረውን ህክምና አጠናቀው፣ በሙሉ ጤንነት ዛሬ ወደ ቢሯቸው ተመልሰዋል። የፕሬዝዳንቱ መመለስ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ከፍተኛ የደስታ ስሜትን የፈጠረ ሲሆን፣ የስራ ባልደረቦቻቸውም “እንኳን ደህና መጡ” በማለት በሞቅ ያለ አቀባበል ተቀብለዋቸዋል።
አቶ አቤ በታመሙበት ወቅት በስልክና በኢሜል ላጠያየቋቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተለይም እርሳቸው ባልነበሩበት ወቅት ስራው ሳይስተጓጎል በስኬት እንዲቀጥል ላደረጉት አመራሮች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
