banner

ቪዥን የጤና አገልግሎት የዳይመንድ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ!

#Fastmereja I ባለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ በምሳሌነት የሚጠቀስ ስራ ሲያከናውን የቆየው ቪዥን የጤና አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ ፣ በግራንድ አፍሪካን (Grand African) የተቋማት ሸልማት ከፍተኛው የዳይመንድ ደረጃ (Diamond Level) የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን ተገለፀ።

ይህ የዳይመንድ ደረጃ ሽልማት ለታካሚዎቻቸዉ በሚሰጡት ልዩ ትኩረት ፣ ለአገልግሎት ጥራት እና ደህንነት ባላቸዉ ጽኑ አቋም፣እንዲሁም ተቋሙ ላለፉት 15 አመታት ላሳየው ቀጣይነት ያለው እድገት እውቅና ለመስጠት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ይህ ተቋም በአሁን ሰአት ከ70 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ እና ድርጅቱ በአሁን ሰአት የክሊኒካል፣የፋርማሲ፣የማማከር፣ የላብራቶሪ፣ የዲያግኖስቲክ እንዲሁም ሌሎች ህክምናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ተቋሙ ባለፉት 15 ዓመታት አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ሲስተም (Digital Healthcare) በመደገፍ የታካሚዎችን መረጃ በአስተማማኝ ሁኔታ መያዝ እንደቻለ እና የምርመራ ውጤቶችን ፈጣን በማድረግ የታካሚዎችን የጥበቃ ጊዜ መቀነሱን የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ስምዖን ሃብተአብ ገልፀዋል።

ቪዥን የጤና ተቋም በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች እንደሚሳተፍ እና ለተለያዩ አቅም ለሌላቸዉ ሰዎች ቅናሽ በማድረግ እና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ለብዙ ሰዎች መድረሳቸዉን የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኮ/ል አማዘ አብርሀ ገልፀዋል።

ድርጅቱ ወደፊት የተቀናጀ የቴሌ መድሀኒት ኔትወርክን፣ በኤ.አይ-ተኮር ክሊኒካዊ የውሳኔ-ድጋፍ ስርአቶችን እና የሞባይል አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ለማዘጋጀት እና የመንግስት እና የግል ሽርክናዎችን በመፈተሽ የተረጋገጠ የዲጂታል ጤና እና የምርመራ አካዳሚ በማቋቋም እና ዘላቂ የፋይናንስ ዘዴዎችን በመፍጠር ተጽእኖውን ከፍ ለማድረግ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ነዉ የተገለፀዉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 በዶ/ር _ ስምኦን ሀብተአብ ተስፋይ የተመሰረተው ቪዢን የጤና አገልግሎት (VHC) ዋና ቅርንጫፉን በአዲስ አበባ በማድረግ አጠቃላይ የህክምና አገልግሎት እና የላቀ የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡





Leave a Comment