0
———————————–
📅 የካቲት 11፣ 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ
የአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ እስከ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ በሦስት አዳዲስ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች በረራ እንደሚጀምርና አዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎችን እንደሚያስመርቅ አስታወቀ።
አየር መንገዱ በረራ የሚጀምርባቸውና አዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎች የተገነቡባቸው ከተሞች፡ ነገሌ ቦረና፣ ጎሬ መቱ፣ ደብረ ማርቆስ ናቸው።
አየር መንገዱ ወደ እያንዳንዱ መዳረሻ በሳምንት ሦስት ጊዜ የመንገደኞች በረራ ለማድረግ አቅዷል። በእነዚህ አዳዲስ መዳረሻዎች አማካኝነት የአየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻ ቁጥር ወደ 26 ከፍ ይላል።
#FastMereja
