banner

“አርሴ ማትችለውን መከላከል ለምን ትመርጣለች?” ሳሚ ዳን

​—————————————-
📅 የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 ሾውቢዝ

​ታዋቂው ድምጻዊ ሳሚ ዳን በክለቡ አርሰናል ወቅታዊ አቋም ላይ ያለውን ስጋትና ጥያቄ በግል የማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ለደጋፊዎች አጋርቷል።
​
አርሰናል አሁን ባለው ሁኔታ የደረጃ ሰንጠረዡ አራተኛ ውስጥ (Top 4) ለመግባት እራሱ ሊያሰጋት እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።

​”በመሀይም የኳስ እውቀቴ ስገመግማት አርሴ ማትችለውን መከላከል ለምን እንደምትመርጥ ግር ይለኛል” ሲል የአሰልጣኙን ስልት ተችቷል።

“አሁን ተስፋችን ፈጣሪ አይደለምን?” በማለትም ነገሮች ከአቅም በላይ እየሆኑ መምጣታቸውን አስፍሯል።

​ሳሚ ዳን ለደጋፊዎቹም “ምታውቁ እስኪ እውቀት ልቀቁብኝ” በማለት ክለቡ ለምን ወደ መከላከል እንደሚያመዝን ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡት ጋብዟል።

​#FastMereja | #Showbiz | #SamiDan | #Arsenal

Leave a Comment