0
#FastMereja I የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአከራካሪ የምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ሕገ-መንግሥቱንና የፕሪቶሪያውን ስምምነት የጣሰ ነው ሲል በጽኑ ኮነነ።
የትግራይ ሕዝብ በከፈለው መስዋዕትነት የተገነባውን ሕገ-መንግሥታዊና ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመጣስ፣ በትግራይ ሕገ-መንግሥታዊ ወሰን ላይ አደጋ የሚጥል ውሳኔ መተላለፉን መግለጫው ገልጿል።
የትግራይ ሕዝብ ድምፅ በሌለበትና ባልተወከለበት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተላለፈው ይህ ውሳኔ፣ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በግልጽ የጣሰ ነው ብሏል።
ይህ “አደገኛ” የተባለው ውሳኔ የሚያስከተለው ዘርፈ-ብዙ መዘዝ ግምት ውስጥ ገብቶ በአስቸኳይ እንዲታረምና ዳግመኛ ግምት እንዲሰጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ በጽኑ ጠይቋል።
#ፖለቲካ መረጃ
