0
#FastMereja I ቴምር ፕሮፐርቲስ፣ የዐቢይ ጾም እና የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቡልጋሪያ አካባቢ አዲስ ባስጀመረው ሳይት አቅራቢያ ለሚገኙ 7ዐ አቅመ ደካማ ዜጎች የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር አካሂዷል።
ቴምር ፕሮፐርቲስ በተለያዩ ጊዜያት የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስ፤ ማዕድ በማጋራት፤ በተለያዩ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሲካሄድም ግንባር ቀደም አጋዥ በመሆን ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ በአራቱም አቅጣጫ የመኖሪያ እና የንግድ ህንጻዎችን በመገንባት ላይ የሚገኘው ቴምር የዜጎችን ከፍተኛ የቤት ፍላጎት ለመመለስ በእጅጉ እየሰራ እንደሚገኝ የቴምር ፕሮፐርቲስ የኢቨንትና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ኡስማን መሀመድ ገልጿል።
ከ10 በላይ አፓርትማዎችን ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲስ 28 ሳይቶች ላይ ግንባታ ላይ ሲሆን በዚህ አመት የሳይቶቹን ቁጥር 100 ለማድረስ አቅዷል፡፡
ከማዕድ ማጋራቱ በተጨማሪ ቀደም ብለው ቤት ለገዙና በእጣ አሸናፊ ለሆኑ ሁለት ደንበኞቹ የሁለት ዘመናዊ የቢዋይዲ (BYD) መኪኖች ቁልፍ ርክክብ አከናዉኗል።




