banner

ድምጻዊ ያሬድ ነጉ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ያለውን አጋርነት ገለጸ፡ “የጊዮርጊስ ዝቅታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድቀት ነው”

​#FastMereja I በቅርቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለታና ግዙፍ ስም ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ “ሊፈርስ ነው” በሚል ሲሰራጭ የነበረውን መረጃ ተከትሎ፣ ታዋቂው ድምጻዊ ያሬድ ነጉ ለክለቡ ያለውን ጥልቅ ፍቅርና አጋርነት ገለጸ።

​ድምጻዊው ባስተላለፈው መልዕክት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክለብነት ባለፈ የአገር ኩራትና የታሪክ ተምሳሌት መሆኑን አውስተዋል። ያሬድ በመልዕክቱ ክለቡ አሁን ያለበትን ፈታኝ ወቅት በጽናት እንዲያልፍ የሞራል ድጋፍ እንደሚሰጥና “ንቅንቅ የለም” በማለት ጥንካሬውን ገልጿል።

​ቅዱስ ጊዮርጊስና ቡና ገበያ የአዲስ አበባ ድምቀትና የኢትዮጵያ ብራንዶች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ክለቡ የማይነካ የአገር ቅርስ መሆኑን አረጋግጧል።

​”ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ አገር ገናና ትልቅ ባለታሪክ ክለብ ነው” ያለው ድምጻዊው፣ የክለቡ መዳከም ለጠቅላላው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድቀት መሆኑን አስገንዝቧል።

​”ይህ ጊዜ አልፎ እናያለን፤ ክፉ አይንካችሁ” ብሏል።

Leave a Comment