banner

ኢራን ሚሳኤል እያዘነበች ነው

#FastMereja I ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባህሬን በሀገሯ የሚገኘው የአሜሪካ የባህር ኃይል 5ኛ ፍሊት ዋና መሥሪያ ቤት በሚሳይል ጥቃት መመታቱን አረጋግጣለች።

ኢራን በአሜሪካና በእስራኤል የተሰነዘረባትን ጥቃት ለመመለስ በባህሬን፣ በኳታር እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ኢላማ ያደረገ የሚሳይል ናዳ ማውረዷን አስታውቃለች።

​በባህሬን ዋና ከተማ መናማ አቅራቢያ በሚገኘው ጁፌር አካባቢ ጭስ ወደ ላይ ሲወጣ መታየቱን የዓይን እማኞች ገልጸዋል። የባህሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎች በቤታቸው እንዲቆዩና ወደ ሰላማዊ ቦታዎች እንዲጠጉ አሳስቧል።

ምንም እንኳን የባህር ኃይሉ ዋና መሥሪያ ቤት መመታቱ ቢገለጽም፣ አብዛኞቹ የአሜሪካ የጦር መርከቦች ከጥቃቱ በፊት ወደ ባህር ወጥተው እንደነበር የሳተላይት ምስሎች ያሳያሉ። አሜሪካ እስካሁን ስለደረሰው ጉዳት ይፋዊ መግለጫ አልሰጠችም።

ኳታር፣ ኩዌት እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የአየር ክልላቸውን በከፊል መዝጋታቸው ተዘግቧል። ኳታር ቢያንስ አንድ የሚሳይል ጥቃት በአየር ላይ ማክሸፏን አስታውቃለች።

Leave a Comment