banner

የኢራኑ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ አሉ ወይስ ተገደሉ?

#FastMereja I የኢራን መንፈሳዊና ከፍተኛ መሪ የሆኑት አያቶላ አሊ ካሜኒ መገደላቸውንና አስከሬናቸውም መገኘቱን የሮይተርስ ዜና አገልግሎት የእስራኤል መገናኛ ብዙኃንን ጠቅሶ ዘገበ።

እንደ ዘገባው ከሆነ፣ አያቶላ አሊ ካሜኒ የተገደሉት በእስራኤልና በአሜሪካ ጥምር ኃይሎች በቴህራን በሚገኘው መኖሪያቸው ላይ በተፈጸመ ጥቃት ነው። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ፣ መሪው “በሕይወት እንደሌሉ የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶች አሉ” ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ የኢራን ባለሥልጣናት ይህንን መረጃ “የሥነ-ልቦና ጦርነት” ሲሉ አስተባብለዋል። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ፣ ከፍተኛ መሪው “በሰላም እና በጤና ላይ ይገኛሉ” ሲሉ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።

Leave a Comment