0
#FastMereja I የአረብ ሊግ ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ ኢራን በኳታር፣ በባህሬን፣ በኩዌት፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በዮርዳኖስ እና በሳውዲ አረቢያ ላይ የሰነዘረችውን የሚሳኤል ጥቃት በጽኑ አውግዟል። ሊጉ ጥቃቱን “በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሀገራት ሉዓላዊነት ላይ የተፈጸመ ግልጽ ጥሰት” ሲል ጠርቶታል።
የአረብ ሀገራት በኢራን እና በምዕራባውያን መካከል ባለው ግጭት ውስጥ እጃቸው ባይኖርም፣ ግዛታቸው ኢላማ መደረጉ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ገልጿል።
እንዲህ ያሉ ድርጊቶች ቀጠናውን ወደማይወጣበት ትርምስ እንደሚከቱትና የዓለም አቀፍ ሰላምን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ አስጠንቅቋል።
ሊጉ ጥቃት ለተፈጸመባቸው አባል ሀገራት ያለውን ሙሉ ድጋፍ በመግለጽ፣ ቀውሱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥሪ አቅርቧል።
