banner

ቴምር ፕሮፐርቲስ ለወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

#FastMereja I ቴምር ፕሮፐርቲስ በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሀግብር ላይ ለፋውንዴሽኑ የ5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

በዚህ ታላቅ የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ላይ የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ቴምር ፕሮፐርቲስ ለፋውንዴሽኑ ካበረከተው የገንዘብ ድጋፍ ባሻገር፣ በመርሀግብሩ ላይ ለተገኙት ከ300 በላይ ለሚሆኑ ወገኖችም የኢፍጣር ግብዣ አድርጓል።

ድርጅቱ በቅርቡ በቡልጋሪያ ሳይቱ ባከናወነው የማስተዋወቂያ መርሀግብር ላይ ለ80 አቅመ ደካሞች ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን የተደረገው የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍም የኩባንያው ተከታታይ የበጎ አድራጎት ስራዎች አካል መሆኑ ተገልጿል።

#ልዩ_ልዩ





Leave a Comment