banner

የፋይን (Fine) የታሸጉ የውሃ ምርቶች ታገዱ!

​#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ በገበያ ላይ የዋሉ (Batch number 620) መለያ ቁጥር ያላቸው የፋይን (Fine) የታሸጉ የውሃ ምርቶችን ማህበረሰቡ እንዳይጠቀም አስጠነቀቀ።

​በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በውሃው ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር የተገኘበት ሲሆን፣ ይህም ለሰው ልጅ ጤና አደገኛ መሆኑ ተረጋግጧል።

​አምራች ድርጅቱ ከየካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱን እንዳያመርትና ወደ ገበያ እንዳያሰራጭ የታገደ ሲሆን፣ በገበያ ላይ ያለውንም በ5 ቀናት ውስጥ እንዲሰበስብ ታዟል።

​ድርጅቱ ምርቱን ሲያመርት የመልካም አመራረት ሥርዓትን ያልተከተለ መሆኑን ባለስልጣኑ አረጋግጫለሁ ብሏል።
​
ማህበረሰቡ ይህንን መለያ ቁጥር (Batch 620) ያለውን ውሃ ከመጠቀም እንዲቆጠብና በገበያ ላይ ሲያገኝም በነጻ የጥቆማ መስመር 8864 ላይ ደውሎ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።

​ድርጅቱ የችግሩን መነሻ ለይቶ አሳውቆና ማስተካከያ ማድረጉ ተረጋግጦ በጽሁፍ ፈቃድ እስካላገኘ ድረስ ምርቱን ማከፋፈል እንደማይችል ተገልጿል።

Leave a Comment