#FastMereja I በልዩ የልግስና ተግባራቱ የሚታወቀው ወጣቱ ባለሀብት ምረትአብ ሙሉጌታ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለሚገጥሙ አቅመ ደካማ ወገኖች በአዲስ መልክ ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች የመጀመሪያ ዙር ርክክብ ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ አከናውኗል።
ለዓመታት ሊወድቁ ተንገዳግደው በነበሩና ለነዋሪዎቹ አስቸጋሪ በሆኑ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ ወገኖች፣ ባለሀብቱ በራሱ ሙሉ ወጪ ቤቶቹን ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ማድረጉ ተገልጿል።
ባለሀብቱ ቤቶቹን ከማስረከብ ባለፈ፣ በአካባቢው ለሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች የምሳ ማብላትና የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በማዘጋጀት ደስታቸውን ተካፍሏል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሰሀረላ አብዱላሂ፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሄራን ገርባ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ታድመዋል።
ወጣት ምረትአብ ሙሉጌታ በምረቃው ላይ ባስተላለፈው መልዕክት፣ ለዚህ በጎ ተግባር ስኬት ፈጣሪን አመስግኖ፤ “ደግነት አይሰለችም” በሚል መርህ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ይህ የዛሬው ርክክብ የመጀመሪያው ዙር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይም በአካባቢው የሚገኙ ሌሎች የተጎሳቆሉ ቤቶችን በማደስ እስከ መጪው የትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል ድረስ ለማስረከብ ቃል ገብቷል።
#ማህበራዊ




