0 #FastMereja I የሀገራችንና የሙስሊሙ ዓለም የክብር ተምሳሌት በሆኑት በንጉስ አል-ነጃሺ ስም የሚገነባው ግዙፍ ኢስላማዊ ማዕከል፣ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ሙሉ ወጪ እንዲገነባ መወሰኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ገለጹ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያበሰሩት “ነጃሺ ለሀገር” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ኢፍጣር አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።