banner

ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ በሩዋንዳ ሁለት ተጨማሪ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አሸነፈች!

#FastMereja I ተወዳጇ ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ በጎረቤት ሀገር ሩዋንዳ በተካሄደ የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ የሁለት ዘርፎች አሸናፊ በመሆን የሀገራችንን ስም በድጋሚ አስጠርታለች።

ቬሮኒካ ሽልማቱን በአካል ተገኝታ ለመቀበል የጉዞ ትኬት ቆርጣ የነበረ ቢሆንም፣ ባልታሰበ ምክንያት መገኘት እንዳልቻለች ገልጻለች። ይሁን እንጂ ሽልማቶቹ በሁለት ቀናት ውስጥ እጇ እንደሚገቡና ለደጋፊዎቿ ልዩ የምስጋና ቪዲዮ ይዛ እንደምትመጣ ቃል ገብታለች።

#ኪነ_ጥበብ

Leave a Comment